ምግብዎ ጤነኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ

(አንዱን ብቻ ይምረጡ፤ ውጤትዎን ከታች ይመልከቱ)

ሀ ለወትሮው በቀን ይሄን ያህል ጊዜ ምግብ ይበላሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ
  • 2 በወር ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ሐ ቁርስዎን ይሄን ይበላሉ

  • 0 የሥጋ ወይም የአንቁላል ጥብስ፣ ወይም በቅቤ የተሰራ ምግብ በየቀኑ
  • 1 ክላይ የተጠቀሰው ምግብ፤ ነገር ግን በሳምንት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ
  • 2 እንጀራ፤ የአበሻ ዳቦ (ቂጣ)፣ ጥራጥሬ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ በየቀኑ ግን በመጠኑ

መ ሥጋ ወይም የሥጋ ወጥ ይሄን ያህል ጊዜ ይበላሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 2 በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ሠ አትክልት ጥራጥሬና ፍራፍሬ ምግቦች ይሄን ያህል ጊዜ ይበላሉ

  • 0 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 1 በየቀኑ
  • 2 በቀን ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ

ረ በዘይት ወይም በቅቤ የተጠበሱ ምግቦች ይሄን ያህል ጊዜ ይበላሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 2 በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ሰ ምግብዎ ውስጥ ይሄን ያህል ጨው ይጨመርልዎታል

  • 0 በደንብ ጠቃ አስከሚል ድረስ
  • 1 በመጠኑ
  • 2 አይጨመርም

ሰ ጣፋጭ ምግቦች ይሄን ያህል ይወስዳሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 2 በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ቀ በቂቤ የተዘጋጀ ምግብ (የገበታ ቅቤ ጭምር) ይሄን ያህል ይመገባሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 2 በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

በ በፈረንጅ ዱቄት (ሲሞሊኖ) የተዘጋጁ ዳቦምች፣ ቂጣዎች፣ ፓስታ፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ምግቦች ይሄን ያህል ይመገባሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 2 በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ተ የሚበሉት ምግብ ይሄን ያህል ነው

  • 0 ጠግበው፤ መብላት አስኪያቅትዎ ድረስ ይበላሉ
  • 1 ጠግበው ሲያበቁ ይነሳሉ
  • 2 ሆድም ለመሙላት ትንሽ ሲቀርዎ ያቆማሉ

ፐ ምግብዎን በይሄን ያህል ፍጥነት ይጨርሳሉ

  • 0 በጣም በፍጥነት
  • 1 በፍጥነት
  • 2 በዝግታ

አ ምግብዎን ሲበሉ

  • 0 በገበታ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመጋራት ነው
  • 1 አልፎ አልፎ ለብቻዎ በሰሃን ይበላሉ
  • 2 ሁል ጊዜ ለብቻዎ በሰሀን ይበላሉ

ነ ከምግብም ጋር ይሄን ይጠጣሉ

  • 0 ጣፋጭ ለስላሳ መጠጦች ወይም የፍራፍሬ ጭማቂ- ሁልጊዜ
  • 1 ጣፋጭ ለስላሳ መጠጦች ወይም የፍራፍሬ ጭማቂ-አልፎ አልፎ
  • 2 የቧንቧ ውሃ፣ በጠርሙስ ተሞልቶ የሚሸጥ ውሃ ወይም ጋዝ ያለው ውሃ

ኘ ይሄን ያህል የአልኮል መጠጥ ይጠጣሉ

  • 0 በቀን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ አስከሚሰክሩ
  • 1 በሳምንት ሦስት ወይም አራት ጊዜ አስከሚሰክሩ
  • 2 በቀን አንድ ወይም ምንም አልጠጣም

ከሀ አስከ ኘ ድረስ ያከበቧቸውን ቁጥሮች በሙሉ ይደምሩ፡: ያገኙት ድምር ከ25 በላይ ከሆነ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ከ20 አስክ 25 ካገኙ ምግብዎ ጥሩ ቢሆንም መሻሻል ያስፈልገዋል፡፡ ከ15 አስክ 19 ካገኙ ምግብዎ አሳሳቢ ነው በጣም መሻሻል ያስፈልገዋል፡፡ ከ15 በታች ከሆነ ምግብም ጤነኛ አይደለምና ጤናዎ በከፍተኛ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይትላል፡፡

ለማንኛውም ስለተመጣጠነ ጤነኛ ምግብና መጠጥ የሚያትተውን ምዕራፍ በማንበብ ምግብዎን ሊያሻሽሉትና ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡

Add new comment