ስለ እውቀት ለጤንነት

ለአገር እድገት ማነቆ ከሆኑ የተለያዩ ምክንያቶች ውስጥ በብዛትና በሰፊ ተንሰራፍተው የሚገኙ በሽታዎችና፣ የጤና ችግሮች እንደ አብይ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ለመከላከል ለመግታት ከተቻለም ለማጥፋት በየቅጣጫው ጥረት እየተደረገ ነው፡: ይህ ጥረት ግቡ እንዲደርስ ስለ ጤና ጠንቆችና መከላከያቸው፤ ስለበሽታዎችና ህክምናቸው እውቀት የቀሰመ ሕዝብና በእነዚህ እውቀቶች ተመርቶ ለጤንነቱ አዎንታዊ እርምጃ የሚወስድ ሕዝብ የግድ ያስፈልጋል፡፡

በመገናኛ ብዙፃን በኩል የጤና እውቀት ወደ ሕዝብ እንዲደርስና እንዲሰርጽ በጤና ዘርፍ የተደራጁ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያላስለሰ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ በዚህ አኳያ የጤና እውቀት በስፊው ለህዝቡ እንዲደርስ የሚደርገውን ጥረትና ድርጊት ለማገዝ ጊዜያቸንንና እውቀታቸንን ለዚሁ ስራ በማዋል ለህዝቡ የሚያስውቁ ፅሐፎችን በማዘጋጀትና በማቅርብና  በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲደርሱ ጥረት እያደረኝ ነው፡፡ ዋና ዓላማችን ስለ ጤንነትና፣ በሽታዎች፣ ስለመከላከያቸውና፣ሕክምናቸው፣ ሕዝቡ በሚረዳውና በሚገባው ቋንቋ እንዲደርሰው በማድረግ እውቀቱ እንዲጎለብትና እንዲስፋ ለማድረግ ነው፡፡ ይህንን ዓላማ ግብ ለማድረስ፤- (ሀ) በሳይንስ ግኝቶች ላይ የተመስረቱና ጊዜያቸው ያላለፈባቸውን የጤናና፣ የበሽታ እውቀቶች ያዘሉ በቀላሉ አንዲገቡ አድርጎ አዘጋጅቶ ማሳተምና ለህዝብ አንዲደርሱ፤ (ለ) ጽሐፎችንና መጽሐፍትን በአማርኛ፣ በኦሮሚፋና፣ በሌሎች የአገሪቷ ቋንቋዎች ለህዝብ በቀላሉ አንዲገቡ አድርጎ አዘጋጅቶ በማሳተም ለህዝብ አንዲደርሱ፤ (ሐ) በእንደዚህ አይነት የተዘጋጁ ጽሐፎችን የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች በነጻ አንዲያገኙና አንዲያሰራጩት እንጥራለን፡፡:

በዚህም መሰረት የአውቀት ለጤንነት መጽሐፍ የመጀመሪያ አትሞች  በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ለአንባብያን ቀርበዋል፡፡ መጽሀፎቹ የሚከተሉት ናቸው
መጽሐፍ 1፡ የአካል፣ የአእምሮና የአዛውንቶች ጤና፤ (መጽሀፎች በኦሮሚፋና በትግሪኛ ተተርጉመው ተሰራጭተዋል)
መጽሐፍ 2፡ የወሲብና የተዋልዶ ጤና (መጽሀፎች በኦሮሚፋና በትግሪኛ ተተርጉመው ተሰራጭተዋል)
መጽሐፍ 3፡ የመተንፈሻ አካላት፣የልብ፣ የደምስር፣ የደም እና የፍርንትት በሽታዎች
መጽሐፍ 4፡ የሆድቃ የአንጀትና የጉበት በሽታዎች
መጽሐፍ 5፡ የአንጎል፣ነርቭ፣ጡንቻ፣አጥንትና መጋጠሚያ በሽታዎች
መጽሐፍ 6፡ የሽንት፣የኩላሊትና የተዋልዶ አካላት በሽታዎች
መጽሐፍ 7፡ የአይን፣ የአፍ ፣ የጥርስ፣ የአፍንጫ፤ የጉሮሮ፣፤ የጆሮ፤ አና ሌሎች የአንገት በላይ በሽታዎች
መጽሐፍ 8፡ የቆዳ በሽታዎች
መጽሐፍ 9፡ የህጻናትና የወጣቶች ጤና
መጽሐፍ 10፡ የህጻናትና የወጣቶች በሽታዎች

እንደበፊቱም እነዚህን መጽሐፍት በኦሮሚፋና፣ በሌሎች የአገሪቷ ቋንቋዎች ለህዝብ ለማቅረብ እቅድ ይዘናል፡፡ ስለ መጽሐፍቱ ያላችሃሁን አስተያየት በኢሜል (info@knowledge4health4ethiopia) በትልኩልን ለምናደርገው የመሻሻል ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል

የመጽሐፎቹ አዘጋጆች

ፕሮፌሰር ደረጀ ከበደ በህክምና የዶክቶሬት ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካገኘ በኋላ በምጽዋና ሚኒሊክ ሆስፒታሎች አገልግሏል፡፡ ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው የፃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በኤፒዲምዮሎጂ (የበሽታዎች ጥናት) የማስትሬትና የዶክቶሬት ዲግሪዎች አግኝቷል፡፡ ከዚያም በአዲስ አበባ ዬኒቨርስቲ የህክምና ፋኩልቲ ውስጥ...
ዶክተር ትዕግስት ቀፀላ በህክምና የዶክቶሬት ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካገኘች በኋላ በዲላና በጅማ ሆስፒታሎች አገልግላለች፡፡ ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ በኤፒዲምዮሎጂ የማስትሬት ዲግሪ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በህፃናት ህክምና የሰፔሻሊስት ዲግሪ አግኝታለች፡: በጤና ጥበቃ...