ዶክተር ትዕግስት ቀፀላ

ዶክተር ትዕግስት ቀፀላ በህክምና የዶክቶሬት ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካገኘች በኋላ በዲላና በጅማ ሆስፒታሎች አገልግላለች፡፡ ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ በኤፒዲምዮሎጂ የማስትሬት ዲግሪ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በህፃናት ህክምና የሰፔሻሊስት ዲግሪ አግኝታለች፡: በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለብዙ አመታት ሰርታለች፡፡: የምርምር ጽሁፎችን ለህትመት አብቅታለች፡፡ ከ1992 ዓም ጀምሮ በአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ ውስጥ በልጆችና አናቶች ጤና ዘርፍ ዳይሬክተር ከዚያም በስዋዚላንድ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ዋና ተጠሪ ሆና ሰርታለች፡: አሁን በታንዛንያ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ዋና ተጠሪ ሆና እየሰራች ትገኛለች፡፡