በየጊዜው በአለማችን ልዩ ልዩ አገሮች የተጠኑ ጥናቶች የሚያመለክቱት በትዳር ውስጥ ያሉ ሰዎች ብቸኛ ከሆኑት ይልቅ የተሻለ ጤንነትና ረዥም አድሜ አንደአላቸው ነው፡፡ ነገር ግን በትዳር ውስጥ መግባባት ከሌለ፤ ከደስታ፣ ከመተሳሰብና ከመፈቃቀር ይልቅ ንትርክ፣ ጠብ፣ መደባደብና አለመተማመን ከሰፈነ ግን ለጤናም ጥሩ አይደለም፡፡ ሕይወትም ሊያሳጥር ይችላል፡፡ ከዚያም አልፎ ለልጆች ደህንነትም አስጊ ነው፤ ለሌላም ቤተሰብ አሳዛኝ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ትዳርዎን መንከባከብ ለእርስዎም፣ ለባለቤትዎ፣ ለልጆችዎና ለሌሎችም ጠቀሜታ አለው፡፡ በትዳር ውስጥ ሳይሆን በፍቅር ጓደኝነት አብረው ያሉም ቢሆኑ ንትርክ፣ ጠብ፣ መደባደብና አለመተማመን ከሰፈነ ለጤና ጥሩ አይደለም፡፡ የትዳር ሆነ የፍቅር ግንኙነትዎ እንዲጎልብት፤ በሌላ በኩል ደግሞ እየተፍረከረከ ከሆነ ለመጠገን ከታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች በመጠቀም እንደገና ሊገነቡት ይችላሉ፡፡
ባሎች፤ ሚስቶች ወይም ፍቅረኞች ፈጽሞ ማድረግ የሌለባቸው
- ለትዳርና ለፍቅር መፍረስ መንስኤ ሊሆኑ ከሚችሉ ድርጊቶች ይቆጠቡ፤
- ከሌላ ሴት/ወንድ የፍቅር ሆነ የወሲብ ግንኙነት አይጀምሩ
- ባለቤትዎን (ፍቅረኛዎን) በቅናት አይጠራጠሩ
- አይናቁ፤ ክብር አይንፈጓቸው
- አይገላመጡ፤ አያዋርዱ፣ አይሳደቡ፣ አይማቱ
- ጥዋት ማታ አይጨቃጨቁ
- ከትዳራችሁ ወይም ከመተዋወቃችሁ በፊት የሆነ ነገር አንዳለፈ ይቁጠሩ፤ በዚያን ጊዜ የሆነ ነገር (መጥፎም ቢሆን) አንስተው ጠብ፤ ጭቅጭቅ፤ ጥል አይፍጠሩ
- መቼም ቢሆን ባለቤትዎን ሆነ ፍቅረኛዎን ከሌላ ወንድ/ሴት ጋር አያወዳድሩ፤ በተለይ ከዘመድዎ፤ ከሌላ ጓደኛዎ ወይም ከድሮ ባለቤትዎ ጋር ፈፅሞ አንዳያወዳድሩ፡፡ የጠብ ምንጭ ይሆናል
- ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) አንድ መጥፎ አጋጣሚ ሲያጋጥማቸውና ለአርሶ ሲነግርዎት ድሮም ነግሬህ/ሽ ነበረ እንዳይሉ፡፡ በጥሞና ያዳምጡ፤ አንደገባዎት ይንገሯቸው፤ ያፅኗኗቸው፤ ያበረቷቷቸው
- በሥራ፣ በትምህርት፤ ወዘተ ሳቢያ ከባለቤትዎ (ከፍቅረኛዎ) እና ከቤተሰብዎ ጋር የሚያሳልፉትን ጊዜ አይቀንሱ፡፡ ከስራዎ/ከትምርትዎ በፊት ለሚወዷቸው ቅድሚያ ይሰጡ፤ በኋላ “ምነው ይሄን ባደረግሁ ኖሮ” ብለው ይቆጮታል
- የመሥሪያ ቤትና የውጪውን ችግርዎን አቤት ይዘው አይግቡ፤ በነዚህ ያልዎትን ንዴት፣ ቁጭት፤ ወዘተ በባለቤትዎ (በፍቅረኛዎ) ላይ አይወጡ፤ ችግርዎን ከባለቤትዎ (ከፍቅረኛዎ) ጋር በአግባቡ መነጋገር መከፋፈል ጥሩ ቢሆንም አርሳቸው ላይ ጫናውን መወርወር፤ ከዚያም አልፎ ልክ እርሳቸው ለችግሩ ተጠያቂ አንደሆኑ አድርጐ መጣላት፣ መጨቃጨቅ፣ መሳደብ፣ ወይም መማታት ፈፅሞ ልክ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለብዎትን ችግር ያለ ንዴትና በርጋታ ለባለቤትዎ (ለፍቅረኛዎ) አስረድተው በግልፅ ምን እየተሰማዎት አንደሆነ ቢነግሯቸው አርሳቸውም ድጋፋቸውን፣ ፍቅራቸውን ይሰጥዎታል
- በጠበቁበት ሰዓት ሳይሆን ቆይተው፣ አርፍደው ወይም አምሽተው ወደ ቤት ወይም ቀጠሮ ቦታ ቢመጡ የት አመሸህ/ሽ የት አረፈድህ/ሽ እያሉ ጭቅጭቅ አያነሱ፡፡ በደስታ፣ በፍቅር ይቀበሏቸው፡፡ በአጠቃላይ ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) ከሥራቸው፣ ከውጪ ወደቤት በደስታ አንዲመጡ፣ እንዲሳቡ ምክንያት ይፍጠሩላቸው
- ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) የወሲብ ግንኙነት ከፈለጉ እምቢ አይበሉ፤ ፍላጎታቸውን ያሟሉላቸው፡፡ ሲያሟሉላቸው ግን በአርስዎም በኩል በስሜት፣ በፍላጐትና በደስታ መሆን አለበት፡፡ አርሳቸው ወሲብ ሲፈልጉ አርስዎ ካልተስማሙ ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) ያንን አርካታ ያላገኘውን ፍላጐታቸውን የሚያካክሱበት ሌላ አማራጭ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ የእርስዎ አምቢታ በሞራላቸው ላይ አሉታዊ ተፅአኖና የህሊና ቁስለት፣ ድቀት ሊደርስባቸው ይችላል፡፡ ይሄ ደግሞ ለትዳራችሁ (ለፍቅራችሁ) ጥሩ አይደለም
ባሎች፤ ሚስቶች ወይም ፍቅረኞች ማድረግ የሚጠበቅባቸው
-
ለባለቤትዎ (ለፍቅረኛዎ) ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ምን ያህል እርሳቸው ለእርስዎ ውድ እንደሆኑ፣ እንዴት በጣም አንደሚወዷቸው ይንገሯቸው
-
የባለቤትዎን (ፍቅረኛዎን) ሞራል በየጊዜው ከፍ ያድርጉላቸው፡፡ ለምሳሌ እንዴት እርሳቸው የሚሠሩት ሥራ ለእርስዎና ለቤተሰቡ ወሳኝ አንደሆነና አንደሚያደንቋቸው ገልፀው አጭር ጽሁፍ አልፎ አልፎ ይላኩላቸው
- መሥሪያ ቤታቸው ደውለው የሥራ ውጥረታቸውን ለመቀነስ በአርስዎ በኩል ለመርዳት ያልዎትን ፍላጐትና <ምን ላድርግ> ብለው ይጠይቋቸው፤ ብልህ፤ አዋቂ፣ አንደሆኑ ይንገሯቸው
- ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) አላማቸው አንዲሳካ፣ አንዲቃናላቸው እርስዎ የሚችሉትን ያህል ይጣሩ፤ ያድርጉ፡፡ በመጀመሪያ የባለቤትዎ ትልቁ ፍላጐት አላማቸው ምን እንደሆነ ይወቁ፤ ያጣሩ፤ ቀጥለው ለመርዳት ፈቃደኝነትዎን ያሳዩ፡፡ ያልተጠየቁትን ምክር ወይም መመሪያ ከመስጠት ይጠንቀቁ፡፡ ነገር ግን በዘዴ የሚያስፈልጋቸውን እርዳታና ድጋፍ ይስጧቸው
- ባገኙት አጋጣሚ ሁሉና በየጊዜው ለእርሳቸው ያልዎትን አድናቆት ይግለጡላቸው፡፡ ስለቁንጅናቸው፣ ስለመልካቸው፤ ስለአይናቸው፣ ስለፀጉራቸው፣ ስለ አዋቂነታችው፤ ስለአስተዋይነታቸው፣ ስለአነጋገራቸው፣ ስለለዛቸው፣ ስለአለባበሳቸው፣ ስለቁመናቸው፣ ስለደግነታቸው፤ ስለጥሩ አናትነታቸው/አባትነታቸው፤ ወዘተ እያነሱ ያሞግሷቸው፡፡ ይሄንን አድናቆትዎን ሌሎች ሰዎች (የባለቤትዎ የእርስዎም ዘመድ/ወዳጆች፣ የሥራ ጓደኞች፤ ወዘተ) ባሉበት በአደባባይ ይግለጡላቸው፡፡ ትንሽ ሊያሳፍራቸውም ቢችልም በጣም ደስ ይላቸዋል፤ በጣም ይወድዎታል
- ከባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) ጋር በቅርበት እስካላችሁ ድረስ እጃቸውን ይያዙ፤ በሰው ፊት ሳያሳፍርዋቸው ይቀፉዋቸው ያሻሽዋቸው፡፡ በተቻለ መጠን በየቀኑ ብዙ ጊዜ ቀረብ አድርገው ይያዝዋቸው፡፡ ነገር ግን በጣም የሚያሳፍራቸውን ከሆነ አያድርጉ
- ፍቅርዎን መግለጫ የሚሆን ስጦታ አርስዎ አራስዎ ከሱቅ ሄደው ገዝተው ይስጧቸው
- ለሚስትዎ (ለሴት ፍቅረኛዎ) የሚሰጡት ስጦታ የፍቅር መግለጫ እንጂ የድጐማ ወይም የማገዣ ስለአልሆነ የቤት እቃ፣ የወጥቤት እቃ፤ ልብስ፤ ወዘተ አይሁን፡፡ ለምሳሌ ሽቶ፣ ቼኮሌት፣ ጌጣጌጥ፣ ፅጌረዳ ጥሩ የፍቅር ስጦታዎች ናቸው
- ለባልዎ (ለወንድ ፍቅረኛዎ) የሚሰጡት ስጦታ ለባለቤትዎ የሚጠቅም መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ ለምሳሌ ሰአት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ክራቫት፣ ቀበቶ ጥሩ ስጦታዎች ናቸው
- በልደታቸው ጊዜ፣ በተጋባችሁበት ቀን አለትና በትላልቅ በዓላት ሁል ጊዜ ሳይረሱ ጥሩ ስጦታ፣ ጥሩ ግብዣ ያድርጉላቸው፡፡ ፍቅርዎንም በተጨማሪ ይግለጡላቸው
- ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ሁለታችሁ ብቻ የምትሆኑበት፤ ከልጆችና ከሌላ ቤተሰብና ጓደኛ ነፃ የሆነ አመቺ ሁኔታ ይፍጠሩ፡፡ ለምሳሌ ምግብ ቤት፣ ሆቴል፣ መናፈሻ፣ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሁለት ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ አብራችሁ ሆናችሁ ተጨዋወቱ፣ ተፋቀሩ
- በየቀኑ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ያህል ከባለቤትዎ ጋር ይነጋገሩ፤ በቀን ምን አንደገጠማቸው ይጠይቋቸው፤ እርስዎም ምን እንዳጋጠምዎት ይንገሩዋቸው
- ሚስትዎ (ሴት ፍቅረኛዎ) ያጋጠማቸውን ችግር ሲነግርዎት በጥሞና ያዳምጡ፤ ችግራቸው አንደገባዎት ለመግለፅ ደግመው ያስተጋቡት፤ አይዞሽ፤ በርቺ ይበሏቸው፡፡ መፍትሄ ካልጠየቁ መፍትሄ ለመሰንዘር አይራሯጡ፤ እርሳቸው የሚፈልጉት ችግራቸውን የሚያዳምጥላቸውና የሚካፈላቸው ሰው ነው
- ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) በአንድ አጋጣሚ አዝነው፣ ተክዘው፣ ተበሳጭተው፤ ወዘተ ለአርሰዎም ባይነግርዎትም ነገር ግን በሁኔታቸው ይሄንን ካወቁ ጊዜ ሳያፈጅ ችግራቸው ምን አንደሆነ ይጠይቋቸው፤ ችግሩን ይጓሯቸው፡፡ እርሳቸው መጋራት ካልፈለጉ ደግሞ ጊዜ ሰጧቸው
- አልፎ አልፎ ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) የሚሉትና የሚፈልጉት ሊለያይ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁል ጊዜ ያግደርድራቸው፡፡ ለምሳሌ የፍቅር መግለጫ ስጦታዎን ሲሰጧቸው አመስግነው “ለሌላ ጊዜ አትቸገር/ሪ” ቢልዎት ስጦታ መስጠት አንዳያቆሙ
- አልፎ አልፎ ብትከራከሩና በሀሳብ ባትግባቡ ችግር የለውም፡፡ ሁለታችሁም ልዩ ልዩ ሰዎች ስለሆናችሁ ይሄ የሚጠበቅ ነው፡፡ በሁለታችሁም የሃሳብ ልዩነት ፍፁም ከሌለ ትዳራችሁ ችግር አለው ማለት ነው፡፡ ወይ ወንድ ወይ ሴት ለጥ ፀጥ በማለት ተገዢ የሆኑና የራስ ሃሳብ የሌላቸው ናቸው ማለት ነው
- ይውጪ ሆነ የውስጥ ጉዳዮችን፤ በተለይ ድርድርና መስማማት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን (ለምሳሌ ገንዘብ ካስፈለግዎትና ከባለቤትዎ ጋር ድርድር አይቀሬ ከሆነ) ከ12 ሰአት፤ ከስራ በኋላ ወይም ምሽት ላይ አታንሱ፤ አትነጋገሩ፡፡ አንዳችሁ ወይም ሁለታችሁም ከስራ በኋላ ድካም ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ጥሩ ድርድር ሊኖር አይችልም
- ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) እርስዎን የሚያስቀይም፣ የሚያናድድ፣ የሚያሳዝን ንግግርና ድርጊት ካደረጉ ወዲያውኑ ከመናገር ይቆጠቡ፤ በችኮላ ወዲያውኑ መናገር፤ በኋላ የሚጸጽትዎ ነገር መናገርና ማድረግ ያስከትላል፡፡ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ ዝም ይበሉ (በማግስቱ ጥዋት ቢሆን ይመረጣል)፤ ስሜትዎ ተረጋግቶ፤ ግራና ቀኙን አመዛዝነው፤ ማለት የፈለጉትን በጥሞና ለመናገር እድል ይሰጥዎታል
- ሁኔታውን በደንብ ያጣሩ፡፡ ለምሳሌ መጥፎ ንግግር ከሆነ ለምን እንደዚያ አንደተናገሩ ይጠይቋቸው
- ያ ንግግር/ድርጊት አንዴት አንዳሳዘንዎት፣ እንዳናደድዎት፤ ወዘተ ግልፅ አድርገው ይንገሯቸው
- ለወደፊቱ ይሄንን ከርሳቸው አንደማይጠብቁ ያሳውቋቸው
- በድርጊታቸው ከተጸጸቱ ወዲያው ይቅር ይበሏቸው፡፡ ካልሆነ ሌላ ዘዴ ይፈልጉ፤ ነገር ግን አየተጐዱ ሰላም ላለማደፍረስ በሚል ሰበብ ዝም አይበሉ
- በሌላ በኩል ደግሞ አርስዎ አጥፍተው ከሆነ ወዲያውኑ ይቅርታ ይጠይቁ
- ከባለቤትዎ (ከፍቅረኛዎ) የሚፈልጉት ነገር ወይም አንዲያደርግልዎት የፈለጉት ነገር ካለ ግለፅ አድርገው ይንገሯቸው፤ ዳር ዳር አይበሉ፤ በቅኔ አይናገሩ፤ ትንሽ ፍንጭ ብቻ ሰጥተው ዝም አይበሉ፤ ላይገባቸው ይችላል፡፡ ብዙ ወንዶች ነገሮች በግልፅ ካልተነገራቸው አይገባቸውም፣ አይረዱም፡፡ ለምሳሌ ወደ ሱቅ ልሄድ ፈልጌ ትራንስፖርት አጥቼ ተቸገርኩ ብለው ከማውራት ይልቅ የእርሳቸውን እርዳታ ከፈለጉ በአርሳቸው መኪና አንዲያደርስዎት በግልፅ ይጠይቋቸው
- ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) የማይወዷቸው ጠባዮች ቢኖሩ፤ የአርስዎ በራስዎ አለመተማመን፣ ስንፍና፣ ቀልድ አለማወቅ፣ ራስ ወዳድነት፣ ቅናት፣ ሰው አለማመን፣ ግድ የለሽነት፣ ክፋትና መመቅኘትን ነው፡፡ እነዚህ መጥፎ ጠባዮች ካሉብዎት ወዲያው ያስወግድዋቸው
- በሌላ በኩል ደግሞ ባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) የሚወዷቸው ጠባዮች ቢኖሩ፤ አዋቂነት፣ አላማና ግብ ያልዎት መሆኑን፤ ጠንካራነት፣ ቆራጥነት፣ በራስ መተማመን፣ ደፋርነት፣ ሩህሩህነት፣ ሃሳቢ መሆንን፣ ቀልድና ጨዋታ ማወቅን፣ ነው፡፡ ስለዚህ በእነዚህ አቅጣጫ አራስዎን ያስተካክሉ
- ውበትዎን ቁንጅናዎን ያስተካክሉ፣ ይጨምሩ፡፡ ወፍራም ከሆኑ ክብደት ይቀንሱ፡፡ ፀጉርዎን በደንብ ይሠሩት፡፡ ጥሩ ጥሩ ልብስ ይልበሱ፡፡ በአጠቃላይ የባለቤትዎን (የፍቅረኛዎን) ቀልብ ለመሳብ ጥረት ያድርጉ፡፡ ከመጋባታችሁ በፊት አርሳቸውን የሳበው ቁንጅናዎ አሁን ካለ ጥሩ፤ ከሌለም መልሰው ያምጡት፤ ማመጣት ይችላሉ
- ሁልግዜ የሰውነትዎን፤ የጫማዎን፣ የአፍዎን ንፅህና እና ጠረን፤ ወዘተ በጥሩ ሁኔታ ላይ አንዳለ ያረጋግጡ
- የአርሳቸውን ቤት መምጣትና በቅርቡ ፍቅራችሁን ለመገላለፅ በናፍቆት ላይ አንደሆኑ ደውለው ይንገራቸው
- ከሥራ ወደ ቤት ሲመለሱ በደስታ በፍቅር ይቀበሏቸው፡፡ የሚያገኙት ቤት ንፁህ የተዘጋጀና ባጠቃላይ ቤት አንዲመጡ የሚጋብዛቸው እንዲሆን ያድርጉ፡፡ የሚጣፍጣቸው ምግብ፣ የሚወዱትን መጠጥ አዘጋጅተው ይጠብቋቸው፡፡ ሙዚቃ ይወዱ አንደሆን የሚወዱትን አይነት አያጫወቱ ይጠብቋቸው
- በጣም ኮስታራ አይሁኑባቸው፤ ቀልድና ጨዋታ ለጤንነትዎ ጥሩ ከመሆኑ በተጨማሪ ለግንኙነታችሁ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የሚያስቁ ነገሮችን ማውራት፣ የሚያስቁ መጽሐፎችን አብራችሁ ማንበብ፣ የሚያስቁ ትያትሮች ሲኒማዎችን ሆነ የቲቪ ፕሮግራሞች አብራችሁ በመመልከት ተደሰቱ፣ ተሳሳቁ፣ ተጫወቱ፣ ተፋቀሩ
- ማታ ማታ አልጋዎ ላይ ከባለቤትዎ (ፍቅረኛዎ) ጋር ሲተኙ (ያለ ውስጥ ልብስ) አርቃንዎን ይተኙ፤ ባለቤትዎም (ፍቅረኛዎም) አርቃናቸውን አንዲተኙ ይገፋፏቸው፡፡ ከበረዳችሁ ብርድልብስ ወይም ጋቢ ጨምሩ፤ ግን አራቁታችሁን፣ ተቃቅፋችሁ ለመተኛት ሞክሩ
- የወሲብ ግኑኝነት ከፈለጉ/ከጠየቁ በኋላ ለሚስትዎ (ለሴት ፍቅረኛዎ) ጊዜ ይስጧቸው፤ የዱብ አዳ አያድርጉባቸው፡፡ ሴቶች ለወሲብ ለመዘጋጀት ቢያንስ 30 ደቂቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይሄም ቢሆን ከላይ የተዘረዘሩትን አንክብካቤዎች ሁሉ በደንብ ካደረጉ ነው፡፡ ያንን ካላደረጉ ግን ባለቤትዎ አስከመጨረሻው ዝግጁ ላይሆኑ ይችላሉ
- ባልዎ (ወንድ ፍቅረኛዎ) ለወሲብ ዝግጁ ሲሆኑ አርስዎም ዝግጁ ይሁኑ፡፡ ከዚያም አልፈው አንዳንዴ በቅድሚያ አርስዎም የወሲብ ፍላጐትዎን ይግለፁ፡፡ የእርሳቸውን ፍቅር፣ አድናቆት፣ ወዲያው ይጐናፀፋሉ
- ቅደመ ወሲብ አንቅስቃሴዎች ያድርጉ፡፡ ጀርባችውን፣ አንገታቸውን፣ አግራቸውን፣ አጃቸውን በቀስታ በዝግታ ፍቅራዊ በሆነ መንገድ ያሻሹ፡፡ በዚያውም አንዴት ቆንጆ እንደሆኑ፣ እንዴት አንደሚወዷቸው ይንገሯቸው
- የወሲብ ግንኙነት ሲያደርጉ፣ አርስዎም አርሳቸውም አንዲደሰቱ፣ አንድትረኩ፣ የተለያየ የወሲብ ዘዴ ይጠቀሙ፡፡ አንዳይሰለችዎ ይጠቅመዎታል፡፡ ለርሳቸውም አንዲሁ
- የወሲብ ስሜት ከፍ የሚልበት ሰዓት በወንድና በሴት ሊለያይ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የወንዶች ስሜት ጥዋት ጥዋት ከፍ ሲል የሴቶች ደግሞ ስሜታቸው ከፍ የሚለው ምሽት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄንን አውቀው የወሲብ ፕሮግራማችሁን ለማስተካክል ይጣሩ
- ከወሲብ ግኑኝነት በኋላ ወንዶች አንቅልፍ አንቅልፍ ሲላቸው፤ ሴቶች ደግሞ አንቅልፋቸው ሊጠፋ ይችላል፤ የባሰ ንቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከግኑንኘነቱ በኋላ ፊትዎን አዙረው ሚስትዎን (ፍቅረኛዎን) ችላ ብለው አያሸልቡ፤ ይቀፏቸው፣ አንዴት አንደተደሰቱ ይንገሯቸው፣ አሁንም እንዴት ቆንጆ አንደሆኑና አርሳቸውን በማግኘትዎ አንዴት እድለኛ አንደሆኑ ይንጓራቸው