ፕሮፌሰር ደረጀ ከበደ በህክምና የዶክቶሬት ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካገኘ በኋላ በምጽዋና ሚኒሊክ ሆስፒታሎች አገልግሏል፡፡ ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው የፃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በኤፒዲምዮሎጂ (የበሽታዎች ጥናት) የማስትሬትና የዶክቶሬት ዲግሪዎች አግኝቷል፡፡ ከዚያም በአዲስ አበባ ዬኒቨርስቲ የህክምና ፋኩልቲ ውስጥ በመምህርነትና በተመረማሪነት ለብዙ አመታት ሰርቷል፡፡ ከ100 በላይ የሚሆኑ የምርምር ጽሁፎችን ለህትመት አብቅቷል፡፡ በ1991 ዓም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝቷል፡፡ ከ1995 እስከ 2009 ዓም ድረስ ብራዛቪል ኮንጎ በሚገኘው በአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ የምርምርና አውቀት ዘርፍ ውስጥ በዛላፊነት ሰርቷል፡፡ ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ቪዚቲንግ ፕሮፌሰር ሆኖ ሰርቷል፡፡ አሁን በአዲስ አበባ ዬኒቨርስቲና ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እያሰተማረ ይገኛል፡፡
