አንቅልፍ ለጤናዎ በጣም አስፈላጊ ነው፡: አካልዎም አእምሮዎም በደንብ አንዲሠሩ፣ ከቀን ድካም በኋላ እንደገና እንዲጠገኑ ምናልባትም ቀን ያየናቸው፤፣ያሸተትናቸው፣፤ የነካናቸው፣ የቀመስናቸው፣፤፣ የሰማናቸው እና ባጠቃላይ ያወቅናቸውን ሁኔታዎቸች/ነገሮች ሁሉ ለዘለቂታው አንዳናስታውሳቸው የሚደረጉበት በእንቅልፍና በህልም ወቅት ነው፡፡: የአንድ ለሊት እንቅልፍ እንኳን ማጣት በሰውነት ላይ ለውጦች ያመጣል፡፡ በሚቀጥለው ቀን ድካምና አንቅልዋፍ- አንቅልፍ ማለትን ያመጣል፡፡ ይፄ ደግሞ የሥራ ውጤትን ይቀንሳል፣ በቤት፣ በሥራ፣ በመንገድ (የመኪና) አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለሰውነታችን በአማካይ ከ7-8 ሰዓት እንቅልፍ ያስፈልገናል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ከዚያ ያነሰ ወይም የበለጠ ሰዓት ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡: አድሜ አየጨመረ ሲሄድ የእንቅልፍ ሰዓት እየቀነሰ ይሄፄዳል፡፡ አድሜያቸው የገፋ ሰዎች፣ የሚያንኮራፉ አና ወፍራም የሆኑ ሰዎች የእንቅልፍ ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ የተወሰኑ ግለሰቦች ደግሞ በእንቅልፍ ጊዜ ት ንፋሻቸው እየተቆራረጠ አየር ስለሚያጥራቸው የሚነቁና በቂ አንቅልፍ ለማግኘት የሚያስቸግራቸውም አሉ፡፡፤ ይህም ሆኖ ብዙውን ጊዜ የአንቅልፍ ችግር የሚያመጡት ዛሳብና ጭንቀት ናቸው፡፡:
ጥሩ አንቅልፍ ለማግኘት የሚከተሉትን ቢያደርጉ ይጠቅምዎታል፡፡
- የሚተኙበትና የሚነሱበትን ሰዓት አለመቀያየር፡፡ እንደዚያ ካደረጉ ሰውነትዎ በቪያ ፕሮግራም መሰረት «የውስጥ ሰዓቱን›› ያስተካክላል፡፡
- ቅዳሜና አሁድ ከወትሮው በላይ ብዙ አርፍደው አይነሱ፡፡
- ቀን ቀን አይተኙ፡: ግድ ከሆነብዎት ከ15 ደቂቃ በላይ አያሸልቡ፡፡
- መኝታ ቤትዎን ለአእንቅልፍና ለወሲብ ግንኙነት ብቻ ያድርጉ፡: ይፄ ማለት ቲቪና ሬዲዮ አዚያ ውስጥ አያስገቡ፡፡ የቤትዎን ሆነ የሥራዎን ጉዳዮች አዚያ ውስጥ አያካሂዚዱ፡፡:
- የመኝታ ክፍልዎ የተመቸ አንዲሆን ያድርጉ:፡: ብርሀን አያብኩዙ፡: ፀጥተኛ ቦታ ይሁን፡፡ ክፍሉ በጣም እንዳይሞቅ እና አንዳይቀዘቅዝ አስፈላጊውን ያድርጉ፡፡:
- የአካል አንቅስቃሴ በየቀኑ ያድርጉ፡:: አንቅስቃሴውን በሚተኙበት ሰዓት አካባቢ አያድርገ፡:
- ከመኝታ በፊት ሻይ፣ ቡና፣ አልኩል አይጠጡ፡፡ ቀለል ያለ ምግብ ይብሉ፡፡ ሲጋራ አያጭሱ፡፡
- ከአንቅልፍዎ አንዳይቀሰቅስምት ከመተኛትዎ በፊት ብዙ ፈሳሽ አይጠጡ፡፡፡
- የወሲብ ግንኙነት ያድርጉ፡: ያዝናናዎታል፡፡ አንቅልፍዎን ያመጣል፡፡
- በሙቅ ውዛሃ ገላ መታጠብ ወይም መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ መዘፍዘፍ ያዝናናል፤ ለአንቅልፍ ይረዳል፡፡
- ከመተኛትዎ በፊት ለአንድ ሰዓት ያህል የፀጥታ ጊዜ ያሳልፉ፡: ከረዥም ሥራ ወይም ጭቅጭቅ በኋላ ለመተኛት አይሞክሩ፡፡
- ወፍራም ከሆኑ ክብደትዎን ይቀንሱ፡!:
- የሚያንኮራፉ ከሆነ ከጀርባ ይልቅ በጐንም ለመተኛት ይሞክሩ፡፡
- ሐኪም ካላዘዘለዎት በስተቀር የእንቅልፍ መድሐኒቶች አይውሰዱ፡፡ ለጊዜው ቢያስተኙም በረዥሙ ሱሰኛ ያደርግዎታል፡፡
- ለመተኛት ከተጋደሙ ክከ15-209 ደቂቃ በኋላ አንቅልፍዎ ካልመጣ አዚያው ተኝተው ለእንቅልፍ ጥረት አያድርጉ፡: ተነስተው መፅሐፍ ያንብቡ፣ ቲቪ ይመልከቱ ወይም አንድ ሌላ ነገር ያድርጉ፡:
አነዚህን ለብዙ ቀናት አድርገው የእንቅልፍ ችግር ካልተጓሻልዎት የአአምሮ ሐኪም ያማክሩ፡፡