አደጋዎች በአብዛኛው ልንከላከላቸው የምንችልና ከመጀመሪያ መኖር የሌለባቸው ናቸው፡: ነገር ግን በየጊዜው ብዙ አደጋዎቹ እየደረሱ ለብዙዎች የሕይወት መጥፋት ወይም የአካል ጉዳት መንሰኤ ይሆናሉ፡:
የአካል ጉዳት በቤት ውስጥ፣ ከቤት ውጪ፤ በመኪና አደጋ፣ በመስሪያ ቤት... ባልታሰበ ሁኔታ ወይም ታቅዶ/ታስቦ ሊደርስብዎት ይችላል፡፡ ለምሳሌ እቤትዎ ውስጥ ባላሰቡት ሁኔታ የረጠበ ወለል አዳልጥዎት ቢወድቁ በአካልዎ ላይ ጉዳት ሊደርስብዎት ይችላል፡፡ ያላሰቡት ያልወጠኑት ነገር ቢሆንም ወለሉ ቢደርቅ ኖሮ፣ እርሰዎም ሁልጊዜ በቤትዎ ወለሎች ደረቅ እንዲሆኑ ቢያደርጉ ኖሮ ምናልባት አደጋውን መከላከል ይቻላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በታሰበ/በተወጠነ ሁኔታ የአካል ጉዳት ሊደርስብዎት ይችላል፡፡ ለምሳሌ በቤትዎ ውስጥ እንዳሉና እንደተኙ ሌቦች ገብተው እቃዎን ከመዝረፍ በላይ እርስዎ ላይ የአካል ጉዳት ወይም አስገድደው የወሲብ ግንኙነት ሊፈጽሙብዎት ይችላሉ፡፡ ከእንደዚህ አይነት አደጋዎችም ቢሆንም የቤተሰብዎን፣ የግቢዎን የደህንነት ጥበቃ በማጠናከር አደጋውን መከላከል ምናልባት ይችላሉ፡፡
ባልታሰበ/ባልተወጠነ መልክ ይሁን በታሰበ/በተወጠነ መልክ የሚደርሱ አደጋዎች ህይወትዎንና ጤናዎን ሊያሳጣዎት የሚችሉ ስለሆነ በቅድሚያ አስበዋቸው ዝግጅት ማድረግ አለብዎት፡:
የመኖሪያ ቤትዎን ለአደጋ አንዳያጋልጥ ማየት፣ ማስተዋል አና አስፈላጊውን ጥንቃቄ መውሰድ ዛላፊነቱ የአርስዎ ነው፡: ከውጪ ተቆጣጣሪ ስለሌለብዎት ይሄንን አርስዎና ቤተሰብዎ ብዙ ጊዜ የሚያሳልፉበትን አካባቢ መቆጣጠር የአርስዎ ተግባር መሆን ይገባዋል፡፡
ከመውደቅ አደጋ መከላከል
ሳያስቡት በመውደቅ ከፍተኛ አደጋ ሊደርስብዎት ይችላል፡፡ የመውደቅ አደጋ ማንም ሰው ላይ ሊደርስ ቢችልም በተለይ በአድሜያቸው ጠና ያሉት ላይ ይዘወተራል፡፡ ከመውደቅ የጭንቅላት ላይ አደጋ፣ የእጅ አንጓ ስብራት፣ የአከርካሪ መሰበር እና የዳሌ መጋጠሚያ ሥብራት ይከተላል፡፡ ቤትዎን ክፍል በክፍል አየዞሩ በመመልከትና አንዳንድ ጥንቃቄዎች በማድረግ ከአንደነዚህ አይነት አደጋዎች ራስዎን መጠበቅ ይትላሉ፡፡:
መታጠቢያ ቤት፡:- ወለሉ ወይም የገላ መታጠቢያ ገንዳ እንዳያዳልጥዎ ይጠንቀቁ፡፡ የማያዳልጥ ንጣፍ ያድርጉ፡: ይሄንን የማያገኙ ከሆነ ነጠላ ጫማ ይጠቀሙ:፡፡ ከባዶ አግር ይሻላል፡፡ መታጠቢያ ቤት ሲጠቀሙ በሩን አይቆልፉት፡: ምናልባት ቢወድቁና ቢጐዱ አንኳን ሌላ ሰው ሊደርስልዎት የሚችለው በሩ ያልተቆለፈ አንደሆነ ነው፡: ምናልባት የሚያስፈልግ ከሆነ መታጠቢያውና መፀዳጀው ጋ የአጅ መያዣ/መደገፊያ ለማሰራት ያስቡ፡:
ወጥ ቤት፡:- ከመደርደሪያ ላይ አቃ ለማውረድ ወንበር ሳጥን የመሳሰሉ ነገሮች አደጋ ላይ ሊጥልዎት ይችትላሉ፡፡: ወለሉ አንዳያዳልጥዎሥ ሁል ጊዜ ደረቅ መሆኑን ያረጋግጡ፡: ወለሉን ሰም አይቀቡ፡፡
መኝታ ቤት፡- ልብስና ሌላ የሚያደናቅፍ ነገር ወለል ላይ አይጣሉ፡፡ ማታ መነሳት ካስፈለግዎ የሚረዳ የራስጌ መብራት ያድርጉ፡: በጣም ረዥም የሆነ አልጋ ላይ ወጥተው አይተኙ፡:
አንግዳ መቀበያ ክፍል፡- ከክፍል ወደ ክፍል ለመተላለፍ አንዲያመች በሆነ መልክ የቤት አቃዎችን ያስተካክሉ፡፡ ትናንሸ አቃዎች፣ የኤሌክትሪክ የስልክ ገመዶች አንዳያደናቅፉ ከመንገድ ላይ ያንሱ፡፡ ምንጣፎች እንዳያደናቅፉ ወይም አንዳይነቃነቁ በማጣበቂያ ከወለሉ ጋር ያያይዚቸው፡፡
ደረጃዎች፡- በደንብ እንዲታዩ መብራት ይገጠምላቸው፡: ደረጃዎች ላይ እቃዎች አንዳይኖሩና እንዳያደናቅፉ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ የአጅ መደገፊያዎች የላሉ አንዳይሆኑ ያረጋግጡ፡: ደረጃዎቹ አንዳያዳልጡ ያድርጓቸው፡፡
በሁሉም የቤት ክፍሎች ውስጥ፡- በአግር ሹራብ ወይም በባዶ አግር ብቻ ቤት ውስጥ ወዲያ ወዲህ ማለት አደገኛ ነው፡: ጫማ ወይም ነጠላ ጫማ (የማያዳልጥ) ያድርጉ፤ ገመድ ካለው እንዳያደናቅፍዎ በደንቡ ይሠሩት:፡: መብራት ድንገት ከጠፋ እንዳይቸገሩ የሚሰራ ባትሪ (ከተጨማሪ ባትሪ ድንጋይ ጋር) በቅርብ ያስቀምጡ፡፡ የኤሌክትሪክ፣ የስልክ አና ሌሎች ገመዶች በግድግዳ ጥግ ጥግ እንጂ ክፍሉን በወለል ላይ አንዳያቋርጡ ያድርጉ፡፡: በአጠቃላይ ቤቱን በፅዳት ይያዙት፡፡ በዝናብ ጊዜ ግቢዎ በተለይም የሚራመዱዋቸው አካባቢዎች አንዳያዳልጥዎ ይጠንቀቁ ፡፡: በደረቅ ጨርቅ ያሰወልውሏቸው፡፡ ሊያደናቅፉ የሚችሉ ከፍተኛ ደረጃዎች ካሉ ብሩህ ቀለም ይቀቡ፡፡ እዚያ አካባቢ መብራት ቢደረግ በምሽት አንዳይደናቀፉ ይረዳል፡፡
የአካል አንቅስቃሴ በተለይም ጡንቻዎችን የሚያጠናክሩ አንቅስቃሴዎች በየጊዜው ቢሠሩ ቢያንስ ሁለት ጥቅም አለው፡፡ ጡነቻዎችዎም ስለሚጠነክሩ በቀላሉ ከመውደቅ ይድናሉ፡: እንቅስቃሴዎቹ አጥንቶችዎን ሰለሚያጠነክራቸው ቢወድቁም አንኳን በቀላሉ አይሠበሩም፡፡
አንደ አጋጣሚ ከወደቁ አይደናገጡ፡፡ ቅርብ ወዳለ ወንበር በመንፏቀቅ ለመነሳትና ለመቀመጥ ይሞክሩ፡፡ የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው አንዲያግዝዎት ይጥሩ፡፡
