ጥርሶችዎ ምግብ ለመፍጨትና ጣዕም ለመስጠት ከሚያደርጉት አስተዋፅኦ ሌላ ለትክክለኛ ንግግርና የአርስዎንም መልክና ማንነት አስከመወሰን ድረስ ሚና አላቸው፡፡: ጥርሶችዎን በንፅህና በጥንቃቂ ካልያዚቸው ሊረግፉ፣ የድድ በሽታ እና ህመም ሊያስከትሉ በተጨማሪም መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡብዎ ይትላሉ፡፡ ከአመታት በፊት ኢትዮጵያኖች የምንታወቅበት የጥርስ ጤንነታችን ቢሆንም አሁን (በተለይም በከተማዎች) እየተሸረሸረና የብዙ ወጣቶችና አዋቂዎች ጥርስና ድድ ከንፅህናና ከአስፈላጊው ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት እየተበላሸ መጥቷል፡፡
ማታና ጥዎት ከምግብ በኋላ ጥርሶችን በእንጨት ወይም በቡሩሽ መፋቅ ከበሽታ ይከላከላል፡፡ በጥርሶች መካከል የሚሰገሰጉ ፍርፋሬዎችንም በመፋቅ የማይለቁ ከሆነ በስንጥር ወይም በቀጭን ክር ተጠቅሞ ማፅዳት ይጠቅማል፡፡
ጣፋጭ ምግቦች የጥርስ ጠንቆች ናቸው፡: ጣፋጭ መጠጦችም (ለስላሳ መጠጦች) እንደዚሁ ለጥርስ አደገኞች ናቸው፡፡ በንግድ ድርጅቶች ያላሰለሰ ማስታወቂያ (ለምሳሌ «የወንጂ ስኳር እንደ ዝሆን ይጠነክራል›› እየተባለ) የጣፋጭ ምግቦች ሥርጭትና አጠቃቀም መጨመሩ ለጥርስ በሽታዎች መበራከት አንዱ ምክንያት ነው፡፡: ልጆችን መጀመሪያውኑ ከጣፋጭ ምግብና መጠጥ ይልቅ ጤናማ የሆኑና አትክልትና ፍራፍሬ አንዲለምዱ ማድረግ ይሄንን ለመከላከል አሰፈላጊ ነው፡፡:
ጣፋጭም ሆነ ሌላ ምግብ ከበሉ በኋላ መፋቅ፣ ይህ የማይቻል ከሆነ ደግሞ ማታና ጥዋት ከምግብ በኋላ ጥርሶችን መፋቅ ፤ በስንጥር ወይም በቀጭን ክር ተጠቅሞ ማፅዳት ከበሽታ ይከላከላል፡፡ ጥርሶችዎን በቡርሽ የሚፋቁ ከሆነ አፋፋቅምዎ በድድዎ ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባዎታል፡፡ ይኸውም የቡርሱሹ እንቅስቃሴ ከላይ ወደ ታች ወይም ከታች ወደ ላይ አንጂ ከአንድ ጐን ወደ አንድ ጐን አለመሆኑን ያረጋግጡ፡፡:
ፍሎሪን የሚባለው ንጥር ነገረ በመጠኑ ሲሆን ጥርስን ለማጠንከርና አንዳይበሰብስም ለመከላከል ያስችላል፡፡ በተፈጥሮም በውሃ ክምችቶች ውስጥ ሊገኝ ስለሚችል አንዳንዶች ከዚህ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይትላሉ፡፡ ‹«መጠነኛ›» የሚባለው በአንድ ሚሊዮን ክፍለ ውሃ አንድ ክፍል ፍሎራይድ (አንድ ፒፒኤም) ሲሆን ከዚህ ካነሰ ለጥርስ ጤና ጥሩ አይደለም:፡: ከ 3 ፒፒኤም ከበለጠ ደግሞ ጥርስ ላይ ቡና አይነት ወይም ጥቋቁር ምልክቶች ይወጣሉ፡፡ በአገራችን በስምጥ ሸለቀው አካባቢ ያለው የውሃ ክምችት ከዚህ በላይ የበዛ የፍሎራይድ መጠን ስለአለው ለጥርስና ለአጥንት አድገትና ጤንነት ጠንቅ ሆኗል፡፡
አርስዎም ሆኑ ቤተሰብዎ የሚጠጡት ውሀ የፍሎራይድ መጠን በልኩ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡: በአካባቢው ያለው የውሀ ልማት ድርጅት ባለሙያዎች ይሄንን መረጃ ሊሰጥዎት ይችላሉ፡፡ ከዚያ በመለስ የሚከተሉትን አርምጃዎች ይውሰዱ፡
የቆሳሻና የበሸታ ህዋሶች በየጊዜው በጥርስ ላይ መጠራቀም ሲበዛ አንደ ርብራብ ሲሚንቶ-መሰል ንጣፍ (ፕላክ ) ይሠራል፡፡ ህዋሶች ጣፋጭ ምግብ ሲያገኙ አሲድ ስለሚፈጥሩ ይህ አሲድ ጥርስን በመብሳት ለሌሎች ህዋሶች ጥርስን አንዲያበሰብሱ መንገድ ይከፍታል፡፡ የፕላክ ጥርቅም ከጥርስም አልፎ የድድ በሽታ ያመጣል፡፡ በድድና በጥርስ መሀል የሚጠራቀመው ፕላክ ድድዎ አንዲቆጣ በማድረግ፣ በጥርስና በድድ መሀል ያለው ግጥም እንዲላላ ያደርጋል፡: ድድም ከጥርሶችዎ አየራቀ ሲሄድ የሚፈጠረው ባዶ ቦታ የበሸታ ህዋሶች መራቢያ ስለሚሆን ጥርሶችዎን ያላላዋል፤ ለጥርስ መውለቅ ምክንያት ይሆናል፡፡
ፕላክ ከመጀመሪያው አንዳይፈጠር በየጊዜው ጥርስዎን መፋቅ፣ በጥርሶችዎና በድድዎም መካከል ትርፍራፊ ምግብ አንዳይኖር በስንጥር ወይም በክር ማውጣት ሲያስፈልግ ስንጥር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ሹል ነገር ሲጠቀሙ ድድዎን እንዳይጐዱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እንደ ገንዘብ አቅምዎ በየስድስት ወሩ በጥርስ ሐኪም በመታየት ፕላክ ከጥርስዎ ላይ ማስለቀቅ በጣም ጥሩና አስተማማኝ የበሽታ መከላከያ እርምጃ ነው፡:
