Blogs

ለውፍረት መፍትሄ

ክብደትዎን ለመቆጣጠር ዋና ዘዴዎቹ፡ ምግብዎን ማስተካከል (ምግብ በልኩ ይሁን፤ ጤናማ ምግብ ይብሉ፤ ምግብ ሲበሉ የካሎሪ መጠን በጥንቃቄ አይተው ይሁን) እና የሰውነት እንቅስቃሴዎን መጨመር ናቸው፡፡

የመደበት ስሜት (ዲፕሬሽን)

የመደበት ፅንሰ ሀሳብ ሀዘን፣ ብስጭት፣ አለመደሰት ወይም መከፋት በሚባሉ አሉታዊ ስሜቶች የሚገለፅ ነው፡፡ አብዛኞቻችን በህይወት ዘመናችን የሆነ ወቅት ላይ ለአጭር ጊዜም ቢሆን በዚህ ስሜት ውስጥ ማለፋችን አይቀርም፡፡ አንድ ሰው የመደበት ችግር ወይም ህመም ተጠቂ ነው የሚባለው ግን የለት ተለት ህይወቱ በሀዘን፣ በብኩንነት፣ በንዴት፣ በመከፋት ወይም በመረበሽ ስሜት ረዘም ላለ ጊዜ የሚታወክበት ከሆነ ነው፡፡

የመደበት ስሜት አብዛኛውን ጊዜ እንደ ክብደቱ ደረጃ የሚለያይ ሲሆን ቀላል፣ መካከለኛ ወይም ከፍተኛ ተብሎ ይለያል፡፡ የችግሩ ክብደት ደረጃም (ይህ በሀኪሙ የሚወሰን ነው) በሚሰጠው ህክምና አይነት ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡

የመደበት ችግር ሦስት ዋና ዋና ገፅታዎች አሉት፤

ምግብዎ ጤነኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ

(አንዱን ብቻ ይምረጡ፤ ውጤትዎን ከታች ይመልከቱ)

ሀ ለወትሮው በቀን ይሄን ያህል ጊዜ ምግብ ይበላሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ
  • 2 በወር ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ሐ ቁርስዎን ይሄን ይበላሉ

  • 0 የሥጋ ወይም የአንቁላል ጥብስ፣ ወይም በቅቤ የተሰራ ምግብ በየቀኑ
  • 1 ክላይ የተጠቀሰው ምግብ፤ ነገር ግን በሳምንት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ
  • 2 እንጀራ፤ የአበሻ ዳቦ (ቂጣ)፣ ጥራጥሬ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ በየቀኑ ግን በመጠኑ

መ ሥጋ ወይም የሥጋ ወጥ ይሄን ያህል ጊዜ ይበላሉ

  • 0 በየቀኑ
  • 1 በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ
  • 2 በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ ያነሰ

ሠ አትክልት ጥራጥሬና ፍራፍሬ ምግቦች ይሄን ያህል ጊዜ ይበላሉ

ከጫት ሱስ መላቀቅ

በአገራችን በሚልዮን የሚቀጠሩ ወንዶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አዋቂዎች ጫት ይቅማሉ፡፡ ጫት ማብቀልም ሆነ መቃም በአገራችን ከተጀመረ በሺህ የሚቆጠር አመታት ሲያስቆጥር በአሁኑ ጊዜ ከተጀመረበት ከምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል ወደ ሌላው በመስፋፋት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና ከተማዎች በሰፊው በጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የበለጠም እየተስፋፋ ነው፡፡ ምንም እንኳን በአንዳንድ ባለሥልጣናትም ሆነ በሃይማኖት መሪዎች ቢወገዝም፣ ስርጭቱንም ለመቀነስ ሙክራ ቢደረግም ጫት መቃም የበለጠ አየተስፋፋ ነው፡፡ በባህል በሐይማኖት ውስጥ ቦታ የተሰጠው መደበኛ ልማድ ከመሆኑም በላይ ለዘመናት የተለያዩ በሽታዎችን ለመፈወሻ እንደ ባህል ሕክምና ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ አሁንም እያገለገለ ነው፡:

Subscribe to RSS - blogs